ወደ ቅድመ ደረጃዎች እንኳን ደህና መጡ!
ኧርሊ ስቴጅስ (Early Stages) ከ 2 ዓመት ከ 8 ወር እስከ 5 ዓመት ከ 10 ወር ለሆኑ ህጻናት የግምገማ (evaluation) ማዕከል ነው። በልጅ ትምህርት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ የዕድገት መዘግየቶችን እና ዕክሎችን (disabilities) እንለያለን። ኧርሊ ስቴጅስ (Early Stages) የዲሲ የኅዝብ ትምህርት ቤቶች (DC Public Schools, DCPS) መርሃ-ግብር ነው። ሁሉም አገልግሎቶቻችን ነጻ ናቸው።