እኛ ከ 2 ዓመት 8 ወር እስከ 5 ዓመት 10 ወር ድረስ ላሉ ሕጻናት የግምገማ ማዕከል ስንሆን፡ ልጅዎ ማንኛውም ዓይነት ዝግመት ካለበት ለመለየት እና ምላሽ ለመስጠት ግልጋሎቶችን እናቀርባለን።
የዲሲ የሕዝብ ት/ቤት ፕሮግራም አካል ስንሆን ማንኛውም ወደ ዲሲ የሕዝብ ት/ቤት ለሚሄድ፤ ከቤት ሆኖ ትምህርት ለሚቀበል፤ እና ገና ት/ቤት ያልገባን ሕጻን ጨምሮ ግልጋሎቶች እናቀርባለን፡ በተጨማሪም ልጅዎ የዲሲ የግል ት/ቤት ቢሄድ ወይም መዋለ ሕጻናት ከሆነ የሚውለው – ከዲሲ ውጪ ቢኖሩ እንኳን ግልጋሎት እንሰጠዎታለን፡ የምንሰጣቸው ግልጋሎቶች ሁሉ ነፃ ናቸው።
የእርስዎ ልጅ ዕድሜው ከ2 ዓመት 8 ወር የሚያንስ ከሆነ እባክዎትን ስትሮንግ ስታርትን ይገናኙ, የዲሲ የቅድመ ተሳትፎ ፕሮግራም ጋር በመደወል (202) 727-3665.
ያሉንን ሁሉ ግልጋላቶች በዋና ቋንቋዎ ምንም ወጪ ሳያወጡ ማግኘት ይችላሉ፡ ይህም የሚያጠቃልለው አስተርጓሚ እንዲቀርብልዎ መጠየቅ እና ማንኛቸውም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎች ወደ ዋና ቋንቋዎ ተተርጉሞ እንዲቀርብልዎት የመጠየቅ መብት አለዎት፡ በቋንቋ ግልጋሎት የማግኛ ድንጋጌ መሰረት ስለመብትዎ በተጨማሪ ለማወቅ.
ወደ እኛ ይምሩ
ወደ ቅድመ ደረጃዎች መምራት በጣም ቀላል ነው፡ እርስዎ ማድረግ ያለበዎት፡
- ልጅዎን ይምሩ [አገናኙን በመጫን]
- ይደውሉልን በ 202-698-8037
- ወደ ማምሪያው ኢሜል ይላኩ [email protected]
በተጨማሪም ከሚቀጥለው ያውሩዱ የመስክ ካርድ[PDF] እና ፋክስ ያድርጉ ወደ (202) 654-6079
ማንም ግለሰብ አንድን ልጅ ወደ ቅድመ ደረጃዎች ሊያመራ ይችላል፡ ቢሆንም ግን ያለወላጅ ወይም አሳዳጊ ፈቃድ እርምጃ አንወስድም፡ ስለ ቅድመ ደረጃዎች ለሌሎች ማካፈል የሚሹ ከሆነ እባክዎትን ነፃነት ይሰማዎ ከሚቀጥለው መምሪያ ቅጽ[PDF]
መብቶቼ ምን ምን ናቸው?
እንደ አንድ የአካል ስንኩል ልጅ ወላጅነትዎ ወይም አሳዳጊነትዎ በልዩ የትምህርት ሥርአት ውስጥ የተወሰኑ መብቶች አለዎት፡ ስለመብትዎ በተጨማሪ ለማወቅ፡ ሥርዓቱ እንዲጠበቅ የሚመለከቱትን ያንብቡ፡
ኦገስት 2018 ሥርዓት እንዲጠበቅ (ሙሉ ጽሁፍ)[PDF]
ምንጮች
በልጅዎ በተለያዩ የእድገት ደረጃዎች ምን መጠበቅ እንዳለብዎ ማወቅ የሚፈልጉ ከሆነ፡ እባክዎትን የሚቀጥሉትን ምንጮች ይመልከቱ።
የእድገት ደረጃዎች [PDF]
የማህበራዊ ስሜታዊ ደረጃዎች [PDF]
ይገናኙን
Walker-Jones Location (ዋከር-ጆንስ የሚገኘው)
1125 New Jersey Ave NW, 3rd Floor
Washington, DC 20001
Phone: 202-698-8037
መኪና ማቆሚያ ነፃ 3-ሰአታ በኤል መንገድ እና በኒው ጄሪሲ ጎዳና ማቆሚያ አለ፡
ባቡር፡ ከ 3 ጣቢያዎች በእግር ርቀት እንገኛለን፡ ማውንት ቭርነር/ኮንቬንሺን ማእከል (አረንጕዴ/ቢጫ መስመር) ዩኒዬን ስቴሽን (ቀይ መስመር) እና ኖማ (ቀይ መስመር)፡ 96 ቁጥር የከተማ አውቶቢስ ከእኛ ሕንጻ ፊት ለፊት ትቆማለች፡ በተጨማሪመ ፒ6 እና ኤክስ2 ቅርብ መቆሚያ አላቸው።
Minnesota Avenue Location (ሚኒሶታ ጎዳና የሚገኘው)
4058 Minnesota Ave NE, Suite 1500
Washington, DC 20019
Phone: 202-442-7201
Fax: 202-654-6079
መኪና ማቆሚያ፡ መንገድ ላይ ሰፈር ውስጥ ማቆም ይቻላል እናም የባቡር መኪና ማቆሚያ ውስጥም (ለመክፈል ስማርት ትሪፕ ካርድ ወይም ክሬዲት ካርድ ብቻ - ገንዘብ አይቀበልም)
ባቡር፡ ከሚኒሶታ ጎዳና የባቡር ጣቢያ አጠገብ ብርቱካናማው መስመር ላይ ሲሆን ማዕከሉ የሚገኘው በተጨማሪም በተለያዩ የአውቶቢስ መስመሮች ማግኘት ይቻላል።
ለአጠቃላይ ጥያቄ፡ [email protected]
ለማምራት፡ [email protected]
ስለ ቅድመ ደረጃዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፡ በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች የተሰጠውን መልስ ይመልከቱ [PDF]